በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜናዊ ካሊፎርኒያ የተቀሰቀሰው ሰደድ እሳት


በሰሜናዊ ካሊፎርኒያ የተቀሰቀሰውን ሰደድ እሳት እያንቀለቀለ ሥፋት ያለው ሥፍራ እንዲያካልል ምክኒያት የሆነው ከባድ አውሎ ንፋስ ረገብ ቢልም፤ በግዛቲቱ ደቡባዊ ክልል የሚገኙ የእሳት አደጋ ተከላካዮች ግን በበኩላቸው የዓየር ትንበያ ባለሞያዎች በዓመታት ውስጥ ከታዩት ሁሉ የበረታ ይሆናል የሚል ግምት በሰጡት እጅግ ከባድ የአውሎ ነፋስ አማካኝነት ከምዕራባዊ ሎሳንጀለስ፣ ሊዛመት ይችል ይሆናል የሚል ሥጋት ላሳደረ የሰደድ እሳት በመዘጋጀት ላይ መሆናቸው ተናገሩ።

ሁለቱም የግዛቲቱ አካባቢዎች በያመቱ በዚህ ወቅት ለሚስተዋለው እጅግ ሞቃታማ እና ደረቅ የዓየር ጠባይ ለቀሰቅሱት እና በካባድ አውሎ ንፋስ አዛማችነት ሠፊ አካባቢ ያካለለ ሰደድ እሳት ለማጥፋት ትንቅንቅ ይዘዋል።

የእሳት አደጋ ሠራተኞች በደቡብ “የጌቲ ቃጠሎ” የሚል መጠሪያ የተሰጠውን እና ሥያሜውን በአቅራቢያው ከሚገኘው ዕውቁ የጌቲ ሙዚየም ያገኘ የሰደድ እሳት እና እንዲሁም በሰሜን ካሊፎርኒያ መጠሪያውን በቅርቡ ከሚገኘው የኪንኬድ ጎዳና የወሰደውን “የኪንኬድ እሳት” እስካሁን 15 በመቶ መቆጣጠር መቻላቸውን በዛሬው ዕለት ይፋ አድርገዋል፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ የሰደድ እሳቶችን በአቅራቢያው በሚገኙ መንገዶች፣ ተቋማትና ታዋቂ ቦታዎች ሥም መሰየም የተለመደ አሰራር ነው።

“የጌቲ እሳት” በዛሬና በነገው ዕለት ብቻ አሁን ከሚገኝበትም ተባብሶ 265 ሄክታር ወደሚሸፍንና አቀጣጣዩም ከባድ ነፋስ በሰዓት 128 ኪሎ ሜትሮች ወደ ሚምዘገዘግ አውሎ ነፋስ ይቀየር ይሆናል የሚል ሥጋት ከዓየር ትንበያ ባለሞያዎች ዘንድ አሳድሯል፡፡

የነፋሱ ፍጥነት በዚህ ከቀጠለ እሳቱን ለማጥፋት የተሰማሩትን ሄሊኮፕተሮች በረራ ሊያግድ እንደሚችል የእሳት አደጋ ባለሥልጣናት አስጠንቅቀዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG