በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከአፍሪካ መሪዎች ጋር ለመገናኘት ወደ አዲስ አበባ አቀኑ


ከትናንት ጀምሮ እስከ መጪው እሁድ ድረስ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ ከሚሳተፉ የሃገራት መሪዎችና ሌሎች አጋሮች ጋር ተገናኝቶ ለመወያየት ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ወደ አዲስ አበባ ማቅናታቸው ተሰምቷል፡፡

የአሜሪካው ልዑካን ቡድን ከአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ጎን ለጎን በአፍሪካ ከሚገኙ አጋሮች ጋር የምግብ ዋስትና በተለይ አፍሪካ ላይ ያስከተለውን ተጽዕኖ በተመለከተ እንዲሁም ባለፈው በዋሽንግተን በተካሄደው የዩኤስ አፍሪካ ጉባኤ ላይ አሜሪካ የገባቸውን ቃል በተመለከተ እንደሚነጋገሩ ታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ግብርናና የአፈር ጤንነት እንዲሁም “መጪውን ትውልድ መመገብ” የተሰኘውን የአሜሪካ ፕሮግራም በተመለከተ ይመክራሉ፡፡

ከአሜሪካው ልዑካን አባላት ውስጥ በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የምግብ ዋስትና ልዩ ልዑክ የሆኑት ዶ/ር ኬሪ ፎውለር፣ በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ጸሃፊ ሞሊ ፊ፣ የዩኤስ አፍሪካ ጉባኤ የፕሬዚዳንቱ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጆኒ ካርሰንና ሌሎችም ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንደሚገኙበት ከዩናይትድ ስቴስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG