በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጦርነት ከተነሳ እስራኤል ውስጥ "አስተማማኝ ቦታ እንደማይኖር" የሂዝቦላህ መሪ አስጠነቀቁ


የሊባኖስ የሂዝቦላህ መሪ ሰይድ ሀሰን ናስራላህ በቴሌቭዥን ቀርበው ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣ በቤሩት ደቡባዊ ዳርቻ
የሊባኖስ የሂዝቦላህ መሪ ሰይድ ሀሰን ናስራላህ በቴሌቭዥን ቀርበው ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣ በቤሩት ደቡባዊ ዳርቻ

በእስራኤል እና በሊባኖስ ታጣቂ ቡድን መካከል ጦርነት ቢቀሰቀስ በእስራኤል ምን አይነት ለደህንነት አስተማማኝ ቦታ እንደማይኖር በሊባኖስ የሚገኘው የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ አስጠንቅቀዋል።

ናስራላህ በቴሌቭዥን ባስተላለፉት መልከዕክት፣ በሁለቱ ጠላቶች መካከል አልፎ አልፎ የሚፈጠረው ግጭት ወደ መጠነ ሰፊ ጦርነት ከተለወጠ፣ በኢራን የሚደገፈው ሂዝቦላህ ጥቃት የሚያደርስባቸው "የኢላማዎች ባንክ" እንዳለው ገልጸዋል።

"እስራኤል ውስጥ ከእኛ ሚላይሎች እና ድሮኖች የተጠበቀ ቦታ አይኖርም" ያሉት ናስራላህ፣ "አዳዲስ የጦር መሳሪያዎች አሉን። ምን እንደሆኑ አንናገርም። ነገር ግን እራሳችንን ለከፋ ነገር እንዳዘጋጀን ጠላታችን ያውቃል። ከኛ ሮኬቶች የሚተርፍ አንድ ቦታ አይኖርም" ሲሉ ተናግረዋል።

እስራኤል ሂዝቦላህ ስላሉት የጦር መሳሪያዎች ጠንቅቃ ታውቃለች ያሉት የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ዋና አዛዥ መቶ አለቃ ጀነራል ሄርዚ ሃሌቪ በበኩላቸው "ጠላት የአቅማችንን ትንሽ ክፍል ብቻ ነው የሚያውቀው እናም በሚያስፈልግ ጊዜ ያያቸዋል" ብለዋል።

በጋዛ ጦርነት ከተነሳበት ከጥቅምት ወር ወዲህ እስራኤል እና የሐማስ አጋር የሆነው ሂዝቦላህ የተወሰኑ ጥቃቶችን ተለዋውጠዋል። ባለፉት ስምንት ወራትም ሊባኖስ ውስጥ ከ400 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን አብዛኞቹ የሂዝቦላህ ተዋጊዎች መሆናቸው እና ቢያንስ 80 ንፁሃን ዜጎችም መገደላቸው ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG