በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኬንያ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ የአራት ሰው ህይወት አለፈ


ሰሜን ምዕራባዊ ኬንያ ውስጥ ሄሊኮፕተር ተከስክሶ አራት አሜሪካውያን እና ኬንያዊው አብራሪ ሞቱ።

ትናንት እሁድ ሄሊኮፕተሩ ከተነሳ ብዙም ሳይቆይ ቱርካና ሃይቅ ላይ ባለ ደሴት ውስጥ በሚገኝ ሴንትራል አይላንድ ብሄራዊ ፓርክ ላይ ሄሊኮፕተሩ መውደቁ የተገለጸው።

የኬንያ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ጊልቤርት ኬቤ ባወጡት መግለጫ ሁለት ሄሊኮፕተሮች ከደሴቱቱ ተነስተው አንደኛው መከስከሱን ገልፀዋል።

ቤተሰቦቻቸው መርዶው እስኪነገራቸው ተብሎ የመንገደኞቹና የኬንያዊው አብራሪ ማንነት ይፋ አልተደረገም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG