በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምስራቃዊ አውስትራሊያ የዘነበ ከባድ ዝናብ በሲድኒ ከተማ ላይ ሥጋት ደቀነ


በብሪስቤን አውስትራሊያ የሚገኝ ህንፃዎች የከባድ ዝናቡ በፈጠረው ጎርፍ አካባቢው ተጥለቅልቆ ይታያል።
በብሪስቤን አውስትራሊያ የሚገኝ ህንፃዎች የከባድ ዝናቡ በፈጠረው ጎርፍ አካባቢው ተጥለቅልቆ ይታያል።

የአውስትራሊያ ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ሲድኒ፤ በሃገሪቱ በጣለ ከፍተኛ ዝናብ የተነሳ የጎርፍ አደጋ እንደሚያሰጋት የአውስትራሊያ ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

ከዛሬ ማምሻውን ጀምሮ እስከ ነገ ሃሙስ ጠዋት ድረስም የ20 ሴ.ሜ ጥልቀት ያለፍ ጎርፍ በምዕራባዊ ሲድኒ እንደሚኖር የተነበዩት ባለሞያዎች የአካባቢው ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ አምስት ሚሊየን ለሚደርሱ የአካባቢው ነዋሪዎች የውሃ አቅርቦት ምንጭ ሆኖ የሚያገለግለው የዋራጋምባ ግድብ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ሞልቶ መፍሰስ መጀምሩም ተገልጿል፡፡

ዝናቡ በተለያዩ የከተማው ክፍሎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ክዊንስላንድ እና ኒው ሳውዝ ዌልስ በተሰኙት ቦታዎች የሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ተወሰኑ ሴንቲሜትሮች ያህል ሰጥመዋል፡፡ እስካሁን ደረስም ከሲድኒ 800 ኪ.ሜትሮች የምትርቀው ሊዝሞር ከተማ የ13 ሰዎች ሕይወት ማለፉ የተገልጸ ሲሆን ከሟቾቹ መካከልም አንድ የ70 ዓመት አዛውንት የሚገኙ ሲሆን የሌላ አንድ ሟች አስክሬን ደግሞ በመሃል ከተማው ሲንሳፈፍ ተገኝቷል፡፡

በሊዝሞር የአደጋ ጊዜ ባለሞያዎች እየጨመረ በመጣው ጎርፍ ምክንያት በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በሚገኙ እና በጣራ ላይ በመውጣት ጭምር እርዳታን ለሚሹ ሰዎች ድጋፍ ለመስጠት እየጣሩ ይገኛሉ፡፡

ሰመር በተሰኘው የአውስትራሊያ ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ ላኒና በተሰነው እና ከባድ ዝናብ በሚያስከትል የአየር ጸባይ የተጋለጠ ነው፡፡

በክዊን ላንድ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የአካባቢ ጥናት ባለሞያ የሆኑት ፕሮፌሰር ሂላቲ ባምብሪክ የአሁኑ ዝናብ ላለፉት አስርት ዓመታት ሳይንቲስቶች በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊፈጠር ስለሚችሉ የአየር ጸባዮች ሲያስጠነቅቁ ቆዩት አደጋዎች አውስትራሊያ አለመዘጋጀቷን ያሳየ ነው ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG