በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳን ውስጥ የደረስ የጎርፍ አደጋ ያስከተለው ጉዳት


ፎቶ ፋይል፦ ብሉ ናይል ካርቱም
ፎቶ ፋይል፦ ብሉ ናይል ካርቱም

ሱዳን ብሉ ናይል ክፍለ ግዛት ውስጥ ቡት የምትባል ከተማ ላይ በደረሰ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ አምስት ሰዎች ሲሞቱ ወደ አንድ ሺህ ሁለት መቶ የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል፤ በአቅራቢያው በሚገኝ ሌላ ዌድ አቡክ የሚባል ከተማም እንዲሁ ከአንድ መቶ ሃያ በላይ መኖሪያ ቤቶች እንደወደሙ ተዘግቧል።

አንድ መቶ ሺህ ነዋሪዎች ባሏት ቡት ከተማ ብዛት ያላቸው ያለመጠጊያ የቀሩ ሴቶችና ህፃናት ደጅ አድረዋል ሲል የሱዳን ቀይ ጨረቃ ማህበር ገልጿል።

የጎርፍ አደጋውን ያስከተለው በከተማዋ የሚገኘው ግድብ በከባድ ዝናብ ምክንያት በመፍረሱ መሆኑን አንድ የአካባቢው ባለሥልጣን ለአሶሽትድ ፕሬስ ገልጿል።

ሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ላይ በጣለው ከባድ ዝናብ አንድ ሺህ የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ መጥለቅለቃቸውን የሃገር ግዛት ሚኒስትሩ ሌተና ጀነራል አልታሪፊ ኢድሪስ ገልጸዋል።

በሃገሪቱ ዙሪያ በጎርፍ ሳቢያ 2380 መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውን ጄነራሉ ጨመረው ገልጸዋል።

ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተገኘ መረጃ መሰረት በአለፈው ዓመት ሃምሌና ነሃሴ ወር ውስጥ ከሃገሪቱ አሥራ ስምንት ክፍለ ግዛቶች በአሥራ ስድስቱ በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሰባ ሳምንት ሰዎች ህይወት አልፏል።

XS
SM
MD
LG