በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቡርኪና ፋሶ መዲና ከባድ የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ወታደሮች ጎዳና ላይ እየታዩ ነው


የቡርኪናፋሶ ወታደሮች በኡጋዱጉ 9/30/2022
የቡርኪናፋሶ ወታደሮች በኡጋዱጉ 9/30/2022

ቡርኪና ፋሶ ውስጥ ዛሬ ዓርብ ከዋናው ወታደራዊ ካምፕና በዋና ከተማዪቱ ከሚገኙ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ከባድ የተኩስ ድምፅና ከፕሬዚዳንቱ መቀመጫ ቤተ መንግሥትም ትልቅ የፍንዳታ ድምፅ መሰማቱን ሮይተርስ ዘገቧል፡፡

ወታደሮቹ ወደ ፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት የሚያመሩትን መንገዶች ላይ ቦታ ቦታቸውን ይዘው የሚታዩ ሲሆን ወደ አስተዳደር ህንፃዎች የሚያመሩ መንገዶችም መዘጋቸው ተነግሯል፡፡

የሃገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥንም አገልግሎት የተቋረጠ ሲሆን የመንግሥት ቃል አቀባይን አግኘቶ ለማነጋገር አለመቻሉን ሮይተርስ አስታውቋል፡፡

እንቅስቃሴው ወታደራዊ መንፈቅለ መንግሥት ስለመሆኑ ግልጽ ባይሆንም ባላፉት ሁለት ዓመታት በምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ የሥልጣን ንጥቂያ ሽኩያዎች ወቅት ከታዩ ሁኔታዎች ጋር ተመሳሳይ ምልክት ያላቸው መሆኑን ዘገባው አመልክቷል፡፡

በኮሌልን ፖል ኼንሪ ሳንዳአጎ ዳሚባ የተመራው ወታደራዊ ጁንታ ሥልጣን የጨበጠው ጥር 16/2014 ዓ.ም በአካሄደው መንፈንቅለ መንግሥት መሆኑ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG