በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም ዙሪያ በልብና ተያያዥ የደም ሥሮች ህመም ዙሪያ ሪፖርት

ፎቶ ፋይል፡- የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም
ፎቶ ፋይል፡- የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም

በዓለም ዙሪያ በልብና ተያያዥ የደም ሥሮች /ካርዲዮ ቫስኪዩላር/ በሚባለው ህመም በካንሰር በስኳር በሽታና በፅኑ የሳምባ በሽታ ሳቢያ ከአሥር ሰዎች ሰባቱ እንደሚሞቱ በቅርቡ “ዘ ላንሴት” በተባለው የህክምና መጽሔት ላይ የወጣ ሪፖርት አስገነዘበ።

በዓለም ዙሪያ በልብና ተያያዥ የደም ሥሮች /ካርዲዮ ቫስኪዩላር/ በሚባለው ህመም በካንሰር በስኳር በሽታና በፅኑ የሳምባ በሽታ ሳቢያ ከአሥር ሰዎች ሰባቱ እንደሚሞቱ በቅርቡ “ዘ ላንሴት” በተባለው የህክምና መጽሔት ላይ የወጣ ሪፖርት አስገነዘበ።

እነዚህ በሽታዎች የሰዎች ካለጊዜያቸው ከመግደላቸውም በተጨማሪ እጅግ ብዙ ገንዘብ የሚያስወጡ መሆናቸውን ሪፖርቱ አመልክቷል።

በሚቀጥሉት አሥራ አምስት ዓመታት ታዳጊ ሀገሮች ከእነዚህ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች በተይያዘ የሚያወጡት ገንዘብ ከሰባት ትሪሊዮን ዶላር እንደሚሆን ተንብየዋል።

ከሦስት ዓመታት በፊት የዓለም መሪዎች እኤአ በ2030 በነዚህ በሽታዎች ያለጊዜያቸው ህይወታቸን የሚያጡትን ሰዎች ቁጥር ለመቀነስ በአንድ ሦስተኛ ለመቀነስ ቃል ገብተው ነበር።

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ትናንት ሃሙስ በመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በአሰሙት ንግግር የተጠቀሰውን ግብ ሊመቱ የሚችሉት ከዓለም ሃገሮች ከግማሽ በታች መሆናቸውን የዓለም መሪዎች የገቡትን ቃል እንዲያድሱ ተማፅኖ አቅርበዋል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG