በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ስድስት ወረዳዎች በአተት ቢያንስ አራት ሰው ሞቷል


በአማራ ክልል ስድስት ወረዳዎች ውስጥ ካለፈው ግንቦት አንስቶ በተከሰተ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ወረርሽኝ ቢያንስ የአራት ሰው ሕይወት ጠፍቷል።

በአማራ ክልል ስድስት ወረዳዎች ውስጥ ካለፈው ግንቦት አንስቶ በተከሰተ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት ወረርሽኝ ቢያንስ የአራት ሰው ሕይወት ጠፍቷል።

ወረርሽኙ በተስፋፋባቸው በአንዳስና በአቡነ ሃራ ገዳም የፀበል ቦታዎች፣ በሰሜን አቸፈር፣ በይልማና ዴንሣ፣ በፍኖተ ሰላም፣ በጎንጅ እንዲሁም ሰሞኑን በደቡብ ጎንደር ስማዳ ወረዳ ቁጥሩ ከ22ዐ በላይ የሆነ ሰው መታመሙን የክልሉ የጤና ቢሮ ገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር አበባው ገበየሁ ለቪኦኤ በሰጡት ማብራሪያ ወቅቱ እንዲሁም እንዲህ ዓይነት ወረርሽኞች ይከሰታሉ ተብሎ የሚሰጋበት ጊዜ መሆኑን ጠቁመው በተለይ ፀበል ለመነከር ወደ ክልሉ ገዳማትና የፀበል ቦታዎች የሚሄዱ ሰዎች እንዲሁም ሕመም ጠንቶባቸው ስለሚደርሱ በቀላሉ እንደሚወድቁ አመልክተዋል።

ቀደም ሲል ከተነገሩት ወረዳዎች በተጨማሪ ባለፈው አንድ ሣምንት ውስጥ በደቡብ ጎንደር ስማዳ ወረዳ ውስጥ 88 ሰው በአተት ተይዞ የሁለት ሰው ሕይወት ማለፉን ገልፀዋል።

ለወረርሽኙ ያለመዘጋጀትና ቸልተኝነት አለ የሚሉ ሰዎችን ክሥ ውድቅ ያደረጉት የጤና ቢሮው ኃላፊ ተወርዋሪ ቡድኖችን ከማሠማራት አንስቶ በየአካባቢውም የተጠናከረ የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ እንደሚከናወን ተናግረዋል።

የተከሰተው ወረርሽኝ ኮሌራ ይሁን አይሁን ለመለየት ምርመራ እንዲደረግ ወደ ማኅበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለላብራቶሪ ምርመራ ናሙና መላኩን ዶ/ር ገበየሁ ጠቁመው ኮሌራ ሆኖ ከተገኘ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደሚነገር ገልፀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በአማራ ስድስት ወረዳዎች በአተት ቢያንስ አራት ሰው ሞቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:57 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG