በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በመኬን ጤና የጤናው ድምፅ ዘገየ


የአሜሪካ የጤና ጉዳይ ከሰሞኑ የዋሺንግተን የፖለቲካ ግለት አካባቢዎች ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡

የአሜሪካ የጤና ጉዳይ ከሰሞኑ የዋሺንግተን የፖለቲካ ግለት አካባቢዎች ጉዳዮች አንዱ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሪፐብሊካን እንደራሴዎች ማሻሻያ የተደረገበት ብለው ያወጡት አዲስ ረቂቅ በዚህ ሣምንት ውስጥ ድምፅ ይሰጥበታል ተብሎ ሲጠበቅ የአሪዞናው ሴናተር ጃን መኬን ድንገት ሆስፒታል በመግባታቸው ምክንያት ተላልፏል፡፡

ይህ ረቂቅ በሕግ መወሰኛ ምክር ቤቱ ሊያልፍ የሚችልባቸው መንገዶች ሁለት ብቻ ናቸው፡፡ አንደኛው፣ በግልፅ የድምፅ ብልጫ ማሸነፍ፤ ሁለተኛውም ደጋፊና ተቃዋሚዎቹ እኩል መከፈል እና በሕጉ መሠረት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ገብተው እንዲገላግሉት መጋበዝ፡፡ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ደግሞ ረቂቁን “በትክክለኛ ጊዜ የመጣ ትክክለኛ ድንጋጌ” ሲሉ ጠርተውታል፡፡

ለማንኛውም እራሣቸውም ቢሆኑ ይደግፉት ይቃወሙት በግልፅ ያልተናገሩትን የጃን መኬንን ወደ ሥራ መመለስ መጠበቁ እንደማይቀር ይፋ ቢሆንም እንደመኬን ሁሉ ያልተቆረጠ ሃሣብ ያላቸው ሌሎችም ሪፐብሊካን እንደራሴዎች መኖራቸው እየተሰማ ነው፡፡

ይህንን የመጨረሻውንና ‘ተሻሻለ’ የተባለውንም ረቂቅ አርባ ስምንቱም ዴሞክራቲክ ሴናተሮች ሙሉ በሙሉ የተቃወሙት ሲሆን “ባለመካከለኛ ገቢ አሜሪካዊያንን የሚጎዳ፣ የቤተሰብ ምጣኔ መርኃግብርን ያለበጀት የሚያስቀር፣ ዕድሜአቸው ከስድሣ ዓመት በላይ የሆነ አሜሪካዊያንን እጅግ ለበዛ ወጭ የሚያጋልጥ ነው” ሲሉ አጣጥለውታል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

በመኬን ጤና የጤናው ድምፅ ዘገየ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:52 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG