በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተዘጋጅተው ነበር የተባሉ ተያዙ


ፎቶ ፋይል፦ ሀዋሳ
ፎቶ ፋይል፦ ሀዋሳ

ሃዋሳ ከተማ ውስጥ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተዘጋጅተው ነበር ያሏቸው ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሲዳማ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል። ግለሰቦቹ የተያዙት ታጥቀዋቸው ነበር ከተባሉ 16 ቦምቦች ጋር መሆኑ ተገልጿል።

የኦሮምያ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ደግሞ “ኦነግ ሽኔ” ብሎ የጠራው ቡድን ከኦሮምያ ክልል የፀጥታ ኃይል ጋር ግልፅ ጦርነት መግጠሙን መናገሩና የሞያሌ አገር አቋራጭ መንገድም ተዘግቷል ማለቱ ሃሰት ነው ሲል አስተባብሏል።

በሌላ በኩል የሲዳማ፣ የኦሮምያና የደቡብ ክልል የፀጥታ ቢሮዎች ከህወሓት ጋር የዓላማ ትብብር በመፍጠር ኢትዮጵያን ለማፍረስ አሲሯል ሲሉ የኮነኑትን እራሱን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” ብሎ የሚጠራውን ቡድን ሸማቂዎች በጋራ ለመመከት ዛሬ ሃዋሳ ከተማ ውስጥ ባካሄዱት መድረክ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።

መንግሥት በሽብርተኛነት የፈረጃቸው ባለሥልጣናቱ “ኦነግ ሸኔ” የሚሉት፤ እራሱን “የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት” የሚለው ቡድንና ህወሓት አብረው ለመንቀሳቀስ መስማማታቸውን ማስታወቃቸው ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ተዘጋጅተው ነበር የተባሉ ተያዙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:20 0:00


XS
SM
MD
LG