በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የወጣቷ መታገት ቤተሰቦቿን አስጨንቋል


የወጣቷ መታገት ቤተሰቦቿን አስጨንቋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:48 0:00

የወጣቷ መታገት ቤተሰቦቿን አስጨንቋል

የሐዋሳ ከተማ ነዋሪ እና የዳሽን ባንክ ሠራተኛ የኾነችው እህታችን ጸጋ በላቸው፣ ከሥራ ወጥታ በኪራይ ወደምትኖርበት ቤት በማምራት ላይ ሳለች ከታገተችብን፣ ዛሬ ዘጠነኛ ቀኗ ቢኾንም፣ የደረሰችበት አልታወቀም፤ ሲሉ፣ ታላቅ እህታቸው ነፃነት በላቸው፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።

የሲዳማ ክልል የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ በበኩሉ፣ ጸጋ በላቸውን ጠልፎ ወስዷል፤ የተባለውን የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ ኮንስታብል የኋላመብራቴ ወልደ ማርያምን ለመያዝ፣ የፖሊስ ቡድን አሠማርቼ አሠሣ እያካሔድኹ ነው፤ ሲል፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል።

በወይዘሪት ጸጋ በላቸው ላይ በተፈጸመው የጠለፋ ወንጀል ጠረጠርኋቸው ያላቸውን ስምንት ሰዎችንም፣ በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያደረገባቸው እንደሚገኝ፣ የቢሮው ሓላፊ አቶ ዓለማየሁ ጢሞቴዎስ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሴቶች የሕግ ባለሞያዎች ማኅበር፣ በጸጋ በላቸው ላይ የተፈጸመውን የመብት ጥሰት እየተከታተለ እንደኾነ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG