በሃዋዪ በአንድ ትልቅ ደሴት ላይ የሚገኝ እሳተ ገሞራ መፍላቱን እና የቀለጠው አለትም መፍሰሱን ቀጥሏል።
እሳተ ገሞራው ከመፈንዳቱ በፊት የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር የአሜሪካው የስነ-ምድር ምርምር ተቋም አስታውቋል።
ኪልዌያ የተሰኘው እሳተ ገሞራ የፈጠረውን ስጋት በመመልከት፣ ተቋሙ የማስጠንቀቂያ ደረጃውን ከፍ አድርጓል።
በ’ሃዋዪ የእሳተ ገሞራ ብሔራዊ ፓርክ’ የሚገኘው የኪልዌያ እሳተ ገሞራ በዓለም ከሚገኙ ከባድ እሳተ ገሞራዎች አንዱ ነው።
በእ.አ.አ 2019 በሥፍራው በደረሰ የመሬት መናወጥ በመቶ የሚቆጠሩ መኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ማዕከላት ፈርሰዋል።
መድረክ / ፎረም