በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሃዋሳ ሃይቅ ስጋትና የባለሞያ ትንታኔ


በውሃናና የአካባቢ ጥበቃ የሲቪል ምህንድስና ባለሞያ የሆኑትንና በበዩናይትድ ስቴትስ በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለሚያቀርብ ተቋም በማገልገል ላይ የሚገኙትን ዶ/ር ስዩም ያሚ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ይሰጣሉ።

በሃዋሳ አዲስ ተሠርቶ ሥራ የጀመረው የኢንዱስትሪ ፓርክ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ከሀይቁ ጋር መገናኘቱ በርካቶችን አሳስቧል ቆይቷል። የኢንደስትሪ ፓርኩ አመራሮች ለአሜሪካ ድምጽ እንደተናገሩት ፓርኩ እጅግ ዘመናዊ በሆነ መልኩ ከፍሳሽ ነፃ ተደርጎ መገንባቱን ገልፀው የፍሳሽ ማስወጃ መስመሩ ለዝናብ ውሃ መውረጃ የተሠራ ነው ብለዋል። የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው የሃዋሳ ዩኒቨርስቲ መምሕራንና ባለሞያዎች ስጋቱ የእነርሱም ጭምር እንደነበር ገልፀው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሩ የተዘረጋው በዝናብ የሚመጣ ፍሳሽን ለማስተላለፍ ብቻ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ይናገራሉ። ሆኖም ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ ከፓርኩ አስተዳደሮች ጋር መመካከራቸውን ይናገራሉ። ይህን ዘገባ ባለፈው ሣምንት ማስደመታችን ይታወሳል።

በዚህ ጉዳይ ሞያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡን በውሃናና የአካባቢ ጥበቃ የሲቪል ምህንድስና ባለሞያ የሆኑትንና በበዩናይትድ ስቴትስ በደቡባዊ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለሚያቀርብ ተቋም በማገልገል ላይ የሚገኙትን ዶ/ር ስዩም ያሚ ጋብዘናቸው ነበር። እኚህ ባለሞያም በፌስቡክ ገፃችን የቀጥታ ስርጭት ቀርበው ሞያዊ ማብራሪያ ሰተወ ነበር።

ለዶ/ር ስዩም ያሚ በመጀመሪያ ያቀረብንላቸው ጥያቄ ከሃዋሳ ኢንደስትሪ ፓርክ ከፋብሪካዎቹ የሚወጣው ፍሳሽ እዛው እንዲቀር እንደሚደረግ መገለፁና ከሀይቁ ቃር የተገናኘው የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ከዝናብ ብቻ ለሚመጣ ፍሳሽ ማስወገጃ በመሆኑ በሃይቁ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት የለም መባሉን ነበር።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ

የሃዋሳ ሃይቅ ስጋትና የማለሞያ ትንታኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:38 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG