በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሲአይኤ ዳይሬክተር ጂና ሃስፐል ሥራ ጀመሩ


የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ተቋም - ሲአይኤ የመጀመሪያዪቱ ሴት ዋና ዳይሬክተር ጂና ሃስፐል ዛሬ ቃለ-መሃላ ፈፅመው ሥራ ጀመሩ።

የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ተቋም - ሲአይኤ የመጀመሪያዪቱ ሴት ዋና ዳይሬክተር ዛሬ ቃለ-መሃላ ፈፅመው ሥራ ጀመሩ።

ከዋና ከተማዪቱ ዋሺንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ በሚገኘው የሲአይኤ ጠቅላይ መሥሪያ ቤት ውስጥ በተካሄደው ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ሚስ ሃስፐልን “ይህቺን ሃገር እጅግ ድንቅ በሆነ ችሎታና መሰጠት ያገለገሉ በጣም ልዩ ሰው” ሲሉ ጠርተዋቸዋል።

ጂና ሃስፐል የሲአይኤ ዳይሬክተር እንዲሆኑ የሕግ ወመሰኛ ምክር ቤቱ ባለፈው ሐሙስ ሹመታቸውን ያፀደቀላቸው 54 ለ 45 በሆነ ድምፅ ነበር።

ሃስፐል ባለፈው ወር ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት የተዛወሩትን የቀድሞ አለቃቸውን ማይክ ፖምፔዮን እንዲተኩ የቀረበውን ሹመት ስድስት ዴሞክራቶች የደገፉ ሲሆን ሁለት ሪፐብሊካን ሴናተሮች ተቃውመውታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG