በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመብት አቀንቃኙ ከያኒ ሀሪ ቤላፎንቴ ሲታወስ


የሲቪል መብቶች ከበሬታ ተሟጋች፣ የፊልም ተዋናይ እና ድምጻዊ ሄሪ ቤላፎንቴ
የሲቪል መብቶች ከበሬታ ተሟጋች፣ የፊልም ተዋናይ እና ድምጻዊ ሄሪ ቤላፎንቴ

ዝነኛው የሲቪል መብቶች ከበሬታ ተሟጋች፣ የፊልም ተዋናይ እና ድምጻዊ ሄሪ ቤላፎንቴ በተወለደ በ96 ዓመቱ አረፈ።

ፈር ቀዳጅ ተዋናይ እና ድምጻዊ በኋላም የመብት ከበሬታ እና የሰብዐዊነት ዕርዳታ ተሟጋቹ ሄሪ ቤላፎንቴ ትናንት ማክሰኞ ኒው ዮርክ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በልብ ድካም ምክንያት ማረፉ ተሰምቷል።

ሄሪ ቤላፎንቴ ለሰብዐዊ መብት ከበሬታ ያለማሰለስ በቁርጠኝነት የታገለ ተሟጋች እና በኪነጥበብ ሥራዎቹም ለአያሌ ሽልማቶች የበቃ የፊልም ተዋናይ እና ድምጻዊ ነበር።

ዜና ዕረፍቱን ተከትሎ የሐዘን መግለጫ እየጎረፈ ነው፡፡ የፊልም ተዋናይቱ ኢቬት ኒኮል ብራውን “የድምጹን ነገር እንዲያው ዝም ነው፡፡ መልከ መልካም የሚያምር ሰውም ነበር፡፡ ልጆቹን በደምብ አሳድጓል፡፡ ዝናን ፈጽሞ ከቆመለት ዐላማ አያስቀድምም ነበር” ብላለች፡፡

በመዝናኛ ኢንዱስትሪው ውስጥ እጅግ ገናናው ጥቁር አሜሪካዊው ተዋናይ ታይለር ፔሪም ሄሪ ቤላፎንቴን በመብት ተከራካሪነቱ ባሳየው ጀግንነት አርአያዬ ነበር” ሲል አድንቆታል፡፡

ብዙ ሚሊዮን የሙዚቃ ቅጂዎች የተሸጡለት ዘፋኝ እና ተዋናይ የነበረው ሄሪ ቤላፎንቴ በኋላ የመዝናኛ ጥበብ ስራዎቹን ጋብ በማድረግ ያለማቋረጥ ጊዜውን ለሲቪል መብቶች እና ለሌሎችም የሰብዐዊነት ስራዎች ሰጥቷል።

የሲቪል መብቶች መሪው የማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ጓደኛ የነበረው ቤላፎንቴ በፖለቲካ መድረኮች እና በጥበብ ባልደረቦቹ ዘንድ አዘውትሮ ይሟገትለት እንደነበር ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG