በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአሜሪካ የምርጫ ጣቢያዎች በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ይዘጋሉ

A large flag hangs from the ceiling as people vote at the San Francisco Columbarium & Funeral Home in San Francisco, Nov. 5, 2024.
A large flag hangs from the ceiling as people vote at the San Francisco Columbarium & Funeral Home in San Francisco, Nov. 5, 2024.

በኢንዲያና እና ኬንተኪ የሚገኙ የተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች በምሥራቅ የሃገሪቱ አቆጣጠር ከምሽቱ 6 ሰዓት ቀድመው ከተዘጉት ውስጥ ሲሆኑ፤ የተቀሩት ደግሞ ከምሽቱ 7 ሰዓት ተዘግተዋል።

25 የሚሆኑ ግዛቶች ደግሞ ከምሽቱ 8 ሰዓት እንደሚዘጉ ይጠበቃል።

በአላስካ ግዛት የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ ከእኩለ ሌሊት በኋላ 1 ሰዓት ላይ ይዘጋሉ።

በበርካታዎቹ ግዛቶች የምርጫውን ውጤት ለማወቅ ሰዓታት፣ ምናልባትም ቀናት ሊወስድ ይችላል።

ሃሰተኛ የቦምብ ጥቃት ዛቻዎች በሚሺጋን፣ ውስከንስን፣ እና ጆርጂያ መሰማታቸውን የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን፣ የአብዛኛዎቹ ዛቻዎች መነሻ ከሩሲያ የተላኩ ኢሜይሎች መሆናቸውንም ቢሮው ገልጿል። በጆርጂያ የሚገኙ ቢያንስ ሁለት ጣቢያዎች ዛቻውን ተከትሎ ሰዎች ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል። የግዛቲቱ ዋና ፀሃፊ ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች ሲሉ ከሰዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG