በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካማላ ሃሪስ ታንዛኒያ አካታች መንግሥት ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት አበረታቱ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ እና ባለቤታቸው ዳግላስ ኤምሆፍ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ እና ባለቤታቸው ዳግላስ ኤምሆፍ

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ የአፍሪካ ጉብኝታቸውንና ለዲሞክራሲ የሚያደርጉትን ግፊት በመቀጠል ዛሬ ሐሙስ ታንዛኒያ ተገኝተዋል፡፡

በሁሉን አካታች መንግሥትነቷ ትታወቅ የነበረችው ታንዛኒያ ወደዛ ለመመለስ ጥረት በማድረግ ላይ በምትገኝበት ወቅት የተገኙት ካማላ ሃሪስ፣ ከአገሪቱ ሴት ፕሬዝደንት ሳሚያ ሱሉሁ ሃሳን ጋር ተገናኝተዋል፡፡

የሁለቱ መሪዎች መገናኘት አሜሪካ ለፕሬዚዳንት ሳሚያ ያላትን ድጋፍ ያመላከታል ተብሏል፡፡

ታንዛኒያ ሁሉን አካታች መንግሥት ለመፍጠር የምታደርገውን ጥረት እንድታጠናከር ካማላ ሃሪስ አበረታተዋል፡፡ በተቃዋሚዎች ሰልፍ እና በፕረስ ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ መደረጉን ካመላ ሃሪስ በበጎ አንስተዋል፡፡

መልካም አስተዳደርን፣ ዘላቂ የኢኮኖሚ አድገትን እና የአየር ንብረት ቀውስን በተመለከተ ተወያይተዋል ተብሏል፡፡

የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በጋና የጀመሩት ካመላ ሃሪስ፣ በአህጉሪቱ የሚያደርጉትን የአንድ ሳምንት ቆይታ ዛምቢያን በመጎብኘት እነድሚያጠናቅቁ ይጠበቃል፡፡

XS
SM
MD
LG