በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካመላ ሄሪስ የሜክሲኮን ድንበር ይጎበኛሉ


ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሄሪስ
ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሄሪስ

ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሄሪስ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ዕጩ ከመሆናቸው ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በአሜሪካና በሜክሲኮ መካከል ያለውን ድንበር ዛሬ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የድንበር ጉዳይ በያዝነው የምርጫ ወቅት እጅግ አከራካሪ ጉዳይ ሲሆን፣ የምክትል ፕሬዝደንቷ ጉብኝት ይህንኑ ጉዳይ ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ያለመ ነው ተብሏል።

በያዝነው የምርቻ ወቅት፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕና አጋራቸው ጄ ዲ ቫንስ ምክትል የባይደን አስተዳደር የድንበር አያያዝ እና እየጨመረ የመጣውን የፍልሰተኞች ጉዳይ በተመለከተ ፕሬዝደንት ካመላ ሄሪስን ካለ ማቋረጥ ሲተቹ ሰንብተዋል።

ሄሪስ በደግላስ፣ አሪዞና የሚገኙ ሲሆን፣ ግዛቲቱ ከሜክሲኮ ጋራ የምትዋሰንና በያዝነው ምርጫም ከፍተኛ ፉክክር ይታይባቸዋል ከሚባሉት አንዷ ነች፡፡

የአሪዞና ግዛት ባልለፈው ዓመት ከፍተና ቁጥር ያላቸው ጥገኝነት ጠያቂዎች የገቡባት ሲሆን፣ የፍልሰተኖች እና የድንበሩ ጉዳይ በዚህ ምርጫ በግዛቲቱ አንገብጋቢ ጉዳዮች ይሆናሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG