በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከማላ ኻሪስ የሰሜን ኮሪያውን አምባገነንነት አወገዙ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ

ደቡብ ኮሪያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስ፣ የሰሜን ኮሪያ “የጭካኔ አምባገነንነትና” “አለመረጋጋትን” ይፈጥራል ያሉትን የጦር መሳሪያዎች መርሃ ግብራቸውን አወገዙ፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ሰሜንና ደቡብ ኮሪያን በሚያዋስነውና ከወታደራዊ ሃይል ነጻ ቀጣና የሆነውን የፓንሙንጆም መንደር ሲጎበኙ ባደረጉት ንግግር “ሰሜን ኮሪያ ውስጥ ጨካኝ አምባገነንነትና በጣም የተንሰራፋ የሰብዊ መብት ረገጣ ህገወጥ እንዲሁም ለሰለምና መረጋጋት ጠንቅ የሆኑ የጦርመሳሪያ መርሃ ግብሮችን” እንመለከታለን ብለዋል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቷ ደቡብ ኮሪያን ከመጎብኘታቸው በፊትና ለጉብኘት በቀጠናው እንደተገኙ ወዲያውኑ ሰሜን ኮሪያ የተወንጫፊ ሚሳኤሎች ሙከራ አድርጋለች፡፡

ሰሜን ኮሪያ በዚህ ዓመት ብቻ 34 የተወንጫፊ ሚሳኤሎችን የተኮሰች ሲሆን ካሁን ቀደም በየዓመቱ ከተኮሰቻቸው ሁሉ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

ከማላ ኻሪስ ሀሙስ ማለዳው ላይ ከደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ዩን ሱክ ዬኦል ጋር አገራቸው ከዩናትድ ስቴትስ ጋር ያላትን ግንኙነት ስለምታሻሻልበት መንገድ መወያየታቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG