በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሀረር ከተማ ገበያ መደብሮች ላይ ለአምስተኛ ጊዜ ከፍተኛ ቃጠሎ ደረሰ


የሀረር ከተማ ገበያ መደብሮች ቃጠሎ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ማክሰኞ የሀረር ከተማ ጸጥ ብላ ዋለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ረቡዕ የክልሉ ፕሬዝዳንት ንብረታቸው የወደመባቸውን አነጋገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ባለፈዉ እሁድ በሐረር ከተማ ሸዋ በር የገበያ ማእከል ለአምስተኛ ጊዜ በደረሰዉ ቃጠሎ ከ700 በላይ የንግድ መደብሮች ወድመዋል። ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በስልክ ስለ ቃጠሎዉ የገለጹ አንዳንድ የንግድ ባለቤቶች በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ብር የሚገመት ኪሳራ እንዳደረሰ ተናግረዋል። መንግስት እሳቱ የተነሳዉ ከአንድ የተዘጋ ምግብ ቤት ዉስጥ ነዉ፤ ይላል። ባለንብረቶቹ ግን የእሳቱ መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን በግልጽ አይታወቅም።

እሳቱ ልክ እንደተነሳ ተመልካቾች ለፖሊስ ቢያሳዉቁም ቃጠለውን ከማጥፋት ይልቅ ተኩስ እያሰሙ ሊያጠፋ የተሰበሰበዉን ሕዝብ መበተን መርጠዋል፤ ሲሉ ከሰዋል። መደብሮቹ ለስምንት ሰዓታት ከነደዱ በኋላ አንዲት አነስተኛ የእሳት አደጋ መከላከያ እንደደረሰች፤ ወዲያዉ እንደጠፋም መንግስት ለግንባታ ቦታዉን በቡልዶዘር መቆፈር እንደ ጀመረ ንብረቴ ወደመ ከሚሉት አንዱ አቶ ገብረ መድህን ገብረ መስቀል ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በስልክ ገልጸዋል። የሀረሪ ክልላዊ መንግስት የኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሪት ሐሰናት አቡበከር በሌላ በኩል እሳቱ የተነሳዉ ከምግብ ቤቱ ዉስጥ መሆኑን የፌዴራሉና የክልሉ ፓሊሶች አረጋግጠዋል፤ ይላሉ።

ከቃጠሎዉ ጋር ተያይዞ በተነሳ ግጭት ከ200 በላይ ሰዎች በፖሊሶች ታስረዉ እንደነበር፥ ይህ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድርስም፥ ለአሜሪካ ድምጽ በቀዉሱ ዙሪያ አስተያየት የሰጡት ባለ ሃብት አቶ ገብረ-መድህን ገብረ-መስቀልን ጨምሮ ቁጥራቸው 150 የሚደርስ ሰዎች እስር ላይ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ጠቁመዋል። የክልሉ መንግስት ግን አቶ ገብረ መድህን የታሰሩት ንብረት በመዝረፍ ተጠቁሞባቸዉ ነዉ፤ ግጭት ሲካሄድ አዉቶቡስ የሰበሩ ሶስት ሰዎች ብቻ ታስረዋል፤ ብሏል። ረቡእ እለት የሀረሪ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙራድ አብዱል ከሪም ንብረታቸዉ ከወደመባቸዉ ሰዎች ጋር ተገናኝተዉ፣ ሱቆቻቸዉን መልሶ ለመገንባት መሬትና ብድር እንደሚሰጣቸዉ መግለጻቸው ተዘግቧል።
XS
SM
MD
LG