በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሐረሪዎች ልዩ ባህላዊ ምግቦች


የሐረሪዎች ልዩ ባህላዊ ምግቦች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00

የሐረሪዎች ልዩ ባህላዊ ምግቦች

በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙት ሀረሪዎች መልከብዙ ባህላዊ ምግቦች አሏቸው። ብሔረሰቡ ለዘመናት ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገሮች ጋር የንግድ ትስስር የነበራቸው በመሆናቸው ሳምቡሳን የመሰሉ ምግቦች ከመካከለኛው ምስራቅ የወረሱት ሲሆን ከቱርኮችም ከባብን የራሳቸው ባህል አድርገዋል። ባጊያ፣ ኩሬባ እና ሰሊጥን የመሰሉ ምግቦችን ከአጎራባች የምስራቅ ኢትዮጵያ ህዝቦች ጋር የሚጋሩት ሲሆን እንጀራ ወይም ኡሃት ደግሞ ከአብዛኛው ኢትዮጵያዊ የሚጋሩት ምግብ ነው። የራሳቸው ብቻ የሆኑ ሌሎች በርካታ ምግቦችም አሏቸው። ብርዝ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር የሚጋሩት ባህላዊ መጠጥ ሲሆን ከሮቃ የሚዘጋጅ የራሳቸው ባህላዊ መጠጥም አላቸው።

አብዛኞቹ ምግቦቻቸው ግን ለገበያ የቀረቡ ባለመሆናቸው በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ እምብዛም አይታወቁም። ባህላዊ ምግብ ቤት የመክፈት ሙከራዎች በድሬዳዋና አዲስ አበባ የነበረ ቢሆንም እንዳልተገፋበት፣ ወደፊት ግን ባህላዊ ምግቦቹ በበርካታ ኢትዮጵያውያን የሚታወቁ እንዲሆንኡ ለገበያ የማቅረብ ስራ እንደሚሰራ የብሔረሰቡ ተቆርቋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG