በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃማስ ሦስት እስራኤላውያን ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል ተጨማሪ እስረኞችን ፈታች


የሃማስ ታጣቂዎች የካቲት 8/2017 ዓ.ም
የሃማስ ታጣቂዎች የካቲት 8/2017 ዓ.ም

ምንም እንኳን ውጥረት እና ስጋት ውስጥ ባለ የተኩስ አቁም ስምምነት መካከል ቢሆኑም፤ እስራኤል ፍልስጤማውያን እስረኞችን ስትፈታ በምትኩ ሃማስ ሦስት ተጨማሪ ታጋቾችን ለቋል።

ከተለቀቁት ታጋቾች አንዱ በደቡባዊ እስራኤል የኪቡትዝ ኒር ኦዝ ነዋሪ የሆነው የ36 ዓመቱ እስራኤላዊ አሜሪካዊ ሳጊ ዴከል ቼን በጎርጎርሳውያኑ ጥቅምት 7 ቀን 2023 በደቡብ እስራኤል በተፈጸመው የሽብር ጥቃት በሃማስ ታጣቂዎች በምርኮ መያዙ ተዘግቧል።

ሁለተኛ የተለቀቀው ታጋች የ29 ዓመቱ እስራኤል-ሩሲያዊው ሳሻ ትሮፋኖቭ ሲሆን ከእናቱ፣ አያቱ እና እጮኛው ጋር አብሮ ነበር የታገተው፤ አባቱ በእገታው ወቅት ተገድሎበታል። ሦስቱ ሴቶች በቀደሙት የታጋች ልውውጦች ተለቀዋል። ሦስተኛው ታጋች ደግሞ ከወንድሙ ጋር አብሮ መታገቱ የተገለጸው አርጀንቲናዊ ኢየር ሆርን የተሰኘ ግለሰብ መሆኑ ተገልጿል።

ሦስቱ ታጋቾች በጋዛ ካኻን ዩኒስ በሚገኘው ለአለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ተላልፈው ተሰጥተዋል። በተመሳሳይ የተፈቱ ፍልስጤማውያንን የጫነ አውቶቡስ ራማላህ ገብቷል። ሃማስ 369 የሚደርሱ ፍልጤማውያን ዛሬ ቅዳሜ እንደሚለቀቁ አስታውቆ ነበር።

የአሁን የእስረኛ እና የታጋቾች ልውውጥ እ.ኤ.አ በጥር 19/2025 በሁለቱ ወገኖች መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት አካል ሲሆን፤ ስድስተኛው ነው።

ሃማስ ታጋቾቹን በ369 ፍልስጤማውያን እስረኞች እና እስረኞች እንቀያየራለን ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG