በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሄይቲ የሽግግር ምክር ቤት ሊቋቋም ነው


ፎቶ ፋይል፦ የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አሪየል ሄንሪ
ፎቶ ፋይል፦ የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አሪየል ሄንሪ

የሄይቲ ጠቅላይ ሚኒስትር አሪየል ሄንሪ ሥልጣናቸውን እንደሚለቁ ማስታወቃቸውን ተከትሎ፣ የአገሪቱ ባለሥልጣናት ሰባት አባላት ያሉት የሽግግር ምክር ቤት ለማቋቋም በዩናይትድ ስቴትስ በተጣለው ቀነ ገደብ ዳር ለማድረስ ጥድፊያ ይዘዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ እና የቀጠናው የካሪቢያን ማኅበረሰብ (ካሪኮም) ያደረጉትን ግፊት ተከትሎ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ መስማማታቸውን ከትላንት በስቲያ ማምሻው ላይ አስታውቀው ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የሄይቲ መዲና ፖርት ኦ ፕሪንስ በአብዛኛው በተቀናቃኝ ወሮ በሎች ቡድን ቁጭር ሥር ስትሆን፣ ግጭቱ በማየሉም ባለፈው እሁድ የአስችኳይ ግዜ አዋጅ ታውጇል። በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎችም መዲናይቱን ለቀው ወጥተዋል።

ካሪኮም ትናንት ሰኞ ጀማይካ ላይ ባደረገው ስብሰባ፣ ሰባት ዓባላት ያለው የሽግ ግር ም/ቤት እንዲቋቋም ሐሳብ አቅርቦ ነበር። የሄይቲ መሪዎችም የተባለውን ም/ቤት እንዲያቋቋሙ የ24 ሰዓታት ጊዜ ተሰጥቷቸው እንደነበር የዜና ወኪሎች ዘግበዋል።

በእቅዱም መሰረት የሽግግር ምክር ቤቱ ስድስት አባላት የተለያዩ የሄይቲ የፖለቲካ ጥምረቶችን የሚወክሉ ሲሆን፣ ሰባተኛው ደግሞ የግል ዘርፉን ይወክላል ተብሏል። በተጨማሪም ድምፅ የመስጠት መብት የማይኖራቸው ሁለት የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮችም በምክር ቤቱ አባልነት እንደሚካተቱ ተጠቁሟል።

ም/ቤቱ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመርጥ ሲሆን፣ ቀጣዩ ፕሬዚደንታዊ ምርጫም እንዲካሄድ ያደርጋል ተብሏል። በተያያዘ ሌላ ዜና፥ ኬንያ ፖሊስ የሚመራና ከአገራት የተውጣጣ ፀጥታ አስከባሪ ኃይል ለመላክ ተይዞ የነበረው እቅድ የኬንያ ባልሥልጣናት ትናንት ማክሰኞ ጊዜያዊው መንግሥት እስኪቋቋም አገራቸው የሰላም አስከባሪ ኃይሏን እንደማትልክ ማስታወቃቸውን ተከትሎ እቅዱን የሚያስለውጥ ሁኔታ ገጥሞታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG