በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሄይቲ አለመረጋጋት ተቃውሞና ዝርፊያ አይሏል


ሄይቲ ውስጥ ነዳጅ ዋጋ መጨመርን አስመልክቶ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ሰንብተዋል፤ 10/3/2022
ሄይቲ ውስጥ ነዳጅ ዋጋ መጨመርን አስመልክቶ ነዋሪዎች ተቃውሟቸውን ሲገልጹ ሰንብተዋል፤ 10/3/2022

ዜጎች በመንግሥት ላይ ያላቸው ምሬት እየጨመረ በመጣባት ሄይቲ ትናንት ሰኞ ከፖሊስ ጋር በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ አንድ ሰው መሞቱ ተገልጿል፡፡

ተቃዋሚዎቹ በዋና ከተማዋ ፖርት ኦ ፕሪንስ በሚገኝ አንድ ሆቴል ላይ ዝርፊያ በሚፈጽሙበት ወቅት የተገደለችውን አንዲ ሴት አስክሬን ተሸክመው ይታዩ እንደበር ተነግሯል፡፡

ሴትዮዋ በፖሊስ መገደላቸውንም ተቃዋሚዎቹ ተናግረዋል፡፡

አመጽ በታኝ ፖሊሶች ድንጋይ የሚወረውሩ ተቃዋሚዎችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝ መጠቀማቸው ተገልጿል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሬል ኼንሪ ሥልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ተቃውሞዎችም በተለያዩ የሄይቲ ግዛቶች መካሄዳቸው ተመልክቷል፡፡

የተፈጠረው የነዳጅ እጥረት፣ ቅሬታና ተስፋ መቁረጥ እንዲባባስ ማድረጉም ተገልጿል፡፡

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በየቦታው የሚካሄድ ዝርፊያ፣ በወሮበላ ቡድኖችና በፖሊሶች መካከል የሚደረግ የተኩስ ልውውጥ በሄይቲ እየተለመደ መምጣቷም ተነግሯል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬሽ ከውንብድና ቡድኖች ጋር እየተጋፈጡ ያሉ የሄይቲ ፖሊሶችን ለመርዳት “ፈጣን ተወርዋሪ ኃይል” የማቋቋም እቅድ ማቅረባቸው ተነገሯል፡፡

ይሁን እንጂ ግን ዋና ፀኃፊው ያንን ኃይል የመንግሥታቱ ድርጅት ያቀርብ እንደሆን አልገለጹም፡፡ የሰው ኃይል ለማቅረብ ፈቃደኝነቱን የገለፀ አገርም እስካሁን አልተገኘም፡፡

XS
SM
MD
LG