ዋሺንግተን ዲሲ —
ሙስናን በሃገራቸው ከሥሩ ለመንቀል እንደሚሠሩ የሄይቲ ፕሬዚዳንት ዦቬኔል ሞዪዝ ዛሬ በድጋሚ ተናግረዋል። ሞዪዝ ይህንን ማረጋገጫ የሰጡት ዛሬ አደባባይ ወጥተው የሃገሪቱ ገንዘብ የት እንደገባ ይጠይቁ ለነበሩ የተቆጡ ሰልፈኞች ባደረጉት ንግግር ነው።
መንግሥታቸው የመንግሥትና የሕዝብን ገንዘብ ያለአግባብ ያወጡና የመዘበሩ ለፍርድ እንዲቀርቡ እንደሚያደርጉዋ ፕሬዚዳንቱ ቃል ገብተዋል።
“ከፍትሕ ማንም አያመልጥም፤ የሞራልና የሕግ ግዴታ ነው” ብለዋል ሥልጣናቸውን በቅርቡ የያዙት የሄይቲው ፕሬዚዳንት።
ወደ አራት ቢሊየን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ የት እንደገባ የሚካሄደው ምርመራ በግልፅ እንዲካሄድ የጠየቁት በሺሆች የሚቆጠሩ ሄይቲያዊያን ናቸው።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ