በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፍና በኬንያ ፖሊስ የሚመራ ኃይል ሄይቲን በማበጥ ላይ ያሉትን ወሮበሎች ለመጋፈጥ ትላንት ማምሻውን መዲናዋ በሆነችው ፖርት ኦ ፕሪንስ ገብቷል።
ሁለት መቶ የሚሆኑ የኬንያ ፖሊስ ኃይል ዓባላት ትላንት ሄይቲ ቢገቡም፣ የመጀመሪያ ተግባራቸው ምን እንደሆነ አለመታወቁን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። ሰማኒያ በመቶ የሚሆንውን የመዲናዋን ፖርት ኦ ፕሪንስ ክፍል የሚቆጣጠሩትን ወሮበሎች እንደሚፋለሙ ይጠበቃል።
ወሮበሎቹ በየመንደሩ ባደረሱት ጥቃት 580 ሺሕ የሚሆኑ ነዋሪዎች ቤታቸውን ጥለው ለመውጣት ተገደዋል።
ወሮበሎቹ እየተጠናከሩ መምጣታቸው የሄይቲን መንግሥት የውጪ ኃይል ዕርዳታ እንዲጠይቅ አስገድዷል።
በሄይቲ የውጪ ኃይል ሲሰማራ ለአራተኛ ጊዜ ነው። ከእ.አ.አ 2004 እስከ 2017 የነበረው የተመድ ልዑክ በጾታ ጥቃትና 10 ሺሕ የሚጠጉ ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈውን ኮሌራን ወደ ሃገሪቱ ይዞ ገብቷል በሚል በመከሰሱ፣ አንዳንድ የሄይቲ ዜጎች የአዲሱን ኃይል መግባት በጥርጣሬ እንዲመለከቱ አድርጓል። አንዳንዶች ግን በመልካም ተቀብለዋቸዋል።
የኬንያ መንግስት የፖሊስ ኃይሉን ወደ ሄይቲ ለማሰማራት መወሰኑ፣ በሃገር ውስጥ የሕግ ንትርክና ተቃውሞ ገጥሞት ነበር።
መድረክ / ፎረም