በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የውጭ ኃይል ገብቶ መብት የሚጥስ ከሆነ እንደሚፋለም የሄይቲ ሁከተኞች መሪ አስታወቀ


በመንደር ስሙ ‘ባርቤክዩ’ እየተባለ የሚጠራው ጂሚ ሼሊዜ የቡድኑ መሪ፣ ለጋዜጠኞች ገለጣ እያደረጉ እአአ ነሃሴ 1/2023
በመንደር ስሙ ‘ባርቤክዩ’ እየተባለ የሚጠራው ጂሚ ሼሊዜ የቡድኑ መሪ፣ ለጋዜጠኞች ገለጣ እያደረጉ እአአ ነሃሴ 1/2023

ሄይቲን “እንዲያረጋጋ” በሚል የሚላክ የውጪ ኃይል መብቶችን የሚጥስ ከሆነ እንደሚፋለመው “የኃይለኛው የወሮበሎች ቡድን መሪ ነው” የሚባለው የቀድሞ የፖሊስ ባልደረባ ዝቷል።

በመንደር ስሙ ‘ባርቤክዩ’ እየተባለ የሚጠራው ጂሚ ሼሊዜ ዜጎች በመንግሥቱ ላይ እንዲነሱ ጥሪ አድርጓል።

የዋና ከተማዪቱን ፖርት-ኦ-ፕራንስን ሰማንያ ከመቶ መቆጣጠራቸው የሚነገረውን ወሮበሎች ለመፋለም ጠቅላይ ሚኒስትር አርየል ኤንሪ የውጭ ዕርዳታ ሲጠይቁ ቆይተዋል።

ኬንያ የፖሊስ ኃይል ልትልክ እንደምትችል የገለፀች ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ በመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ከድርጅቱ ውጭ የሆነ ኃይል መሠማራት የሚያስችል የውሳኔ ሃሳብ ለማስፀደቅ ማሰቧ ተገልጿል።

ዓለም አቀፉ ኃይል ጠቅላይ ሚኒስትሩንና “ሙሰኞች” የሚላቸውን ፖለቲከኞች ለመያዝ የሚመጣ ከሆነ እንደሚቀበል ‘የወሮበሎቹ መሪ ነው’ የሚባለው ሼሊዜ ገልጿል።

ኤንሪ በትረ ሥልጣኑን የጨበጡት የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ዦቨኔል ሞዪስ ከሁለት ዓመታት በፊት በአደጋ ጣዮች መገደላቸውን ተከትሎ ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG