ፈረንሣይ 170 የሚሆኑ ዜጎቿን በወሮበሎች በመናጥ ላይ ካለችው ሄይቲ ማስወጣቷን የአገሪቱ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ረቡዕ አስታውቋል። በፈረንሣይ ወታደራዊ ሄሊኮፕተር በተከናወነው ዜጎችን የማስወጣት ሥራ፣ 70 የሚሆኑ የሌሎች አገራት ዜጎችም እንደተካተቱ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።
ሰዎቹ በአካባቢው ወደሚገኘው የፈረንሣይ የባሕር ኃይል መርከብ ተዛውረው፣ በኋላም ማርቲኒክ ወደተሰኘችው የፈረንሣይ ግዛት እንደሚወሰዱ ታውቋል።
አብዛኞቹ ጥንድ ዜግነት ያላቸው አንድ ሺሕ የሚሆኑ ፈረንሣውያን በሄይቲ እንደሚኖሩ የፈርንሣይ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የሄይቲ መዲና ፖርት ኦ ፕሪንስ በአብዛኛው በወሮበሎች ቁጥጥር ሥር ስትሆን፣ ባለፈው የካቲት በመካከላቸው የተነሳውን ውጊያ ተከትሎ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አሪየል ሄንሪ ሥልጣናቸውን ለቀዋል። ጠቀላይ ሚኒስትሩ ከሥልጣን የለቀቁት የወሮበሎቹ ጥምረት በጠየቀው መሠረት መሆኑ ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥልጣናቸውን ቢለቁም ሁለቱ ጋብ አላለም።
አዲስ የሽግግር መንግሥት እንዲቋቋም በመጠበቅ ላይ ያሉት የአገሪቱ ዜጎች፣ በከፍተኛ የምግብ እጥረት በመቸገር ላይ መሆናቸው ታውቋል።
መድረክ / ፎረም