በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰበር ዜና:- ኃይሉ ሻወል አረፉ


አቶ ኃይሉ ሻወል
አቶ ኃይሉ ሻወል

ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲና ከመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ መሥራቾችና መሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ ኃይሉ ሻወል አረፉ፡፡

ከቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲና ከመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት - መኢአድ መሥራቾችና መሪዎች አንዱ የነበሩት አቶ ኃይሉ ሻወል አረፉ፡፡

አቶ ኃይሉ ሻወል በሰማንያ ዓመት ዕድሜአቸው ዛሬ ያረፉት በሕክምና ሲረዱ በነበረባት ታይላንድ መሆኑን ለቪኦኤ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል፡፡

አቶ ኃይሉ ሻወልን ለሕልፈት ያበቃቸው የጤና ችግር ምን እንደሆነ ለጊዜው እያጣራን ቢሆንም እራሣቸው በፃፉት መፅሐፍ ላይ እሥር ቤት ሣሉ በገጠማቸው ቅዝቃዜ ምክንያት አከርካሪያቸው ላይ ሕመም ይሰማቸው እንደነበረ ጠቁመዋል፡፡

ላለፉት ሁለት ዓመታትም በብርቱ ሲታመሙ መቆየታቸው ተገልጿል፡፡

የአቶ ኃይሉ ሻወል (ኢንጂነር)አስከሬን ነገ፤ ዓርብ አዲስ አበባ ይገባል ተብሏል።

ተጨማሪ መረጃ ባገኘን ጊዜ ይህንን ዜና እናዳብራለን፡፡ በነገ የአየር ሥርጭታችን ላይ ሥፋት ያለው ዘገባ ለማቅረብ እንጥራለን፡፡

XS
SM
MD
LG