አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በቃታር ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዶሃ ገብተዋል። ሼኽ መሃመድ አል አሙዲ አልተፈቱም።
ጉብኝቱ የሁለቱን ሃገሮች ግንኙነቶች ለማጠናከር የታሰበ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለቪኦኤ ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ቁጥጥር ሥር የሚገኙት ትውልደ-ኢትዮጵያ ቢሊዬነር ሼኽ መሃመድ ሁሴን አል-አሙዲ ተፈትተዋል የሚል ወሬ በዌብሳይቶች ላይ ቢሠራጭም መረጃው የተሣሣተ ነው ሲሉ አቶ መለስ አክለው አመልክተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ