ድሬዳዋ —
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሙላቱ ተሾመ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ፣ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የበዓሉ ተካፋይ ሆነዋል።
ከዚህ በተጨማሪም የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽር የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ እና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ መሐሙድን ጨምሮ የበርካታ ሃገራት ተወካዮች እና ዲፕሎማቶች በበዓሉ ላይ ተገኝተዋል።
ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ተወካዮች ባህላዊ ትርዒት አሳይተዋል።
የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በሁላችንም ልብ ውስጥ ሊሰርፅ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥሪ አቅርበዋል፤ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የራሳቸው ማንነት ያላቸውን ያህል፣ የጋራ የሆነ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ማንነትም አላቸው ሲሉ ተናግረዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡