በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኃይሌ ይሮጣል


ኃይሌ ወደ ሩጫው ተመልሷል፡፡ ሩጫ ለማቆም ደርሶበት የነበረውን ውሣኔ በኒው ዮርክ ማራቶን በገጠመው ሕመም ምክንያት በስሜታዊነት የተናገረው እንደነበርም አስታውቋል፡፡

ውሣኔውን የወሰነው "ሃገር ውስጥ በሚደርስበት ፖለቲካዊ ጫና ምክንያት ነው" በሚል "ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ" የሚባለው የዩናይትድ ስቴትስ ዕለታዊ ጋዜጣ የዘገበውን አስተባብሏል፡፡

ኃይሌ በዝምታ ከቆየ በኋላ ይህንን መግለጫ የሰጠው ዓርብ ኅዳር 10 ቀን በሒልተን ሆቴል በሰጠው መግለጫ ነው፡፡ ኒው ዮርክ ላይ የተካሄደው ማራቶን የፈጠረበት ስሜት ለውሣኔው ምክንያት እንደነበረ ተናግሯል፡፡

ለኒው ዮርክ ማራቶን ተዘጋጅቶ መሄዱን የጠቆመው ኃይሌ ጉልበቱ ላይ የነበረው ሕመም ቀደም ባለው ቀን መባሱንና እንዲያውም ማበጡን ጠቁሟል፡፡ ውድድሩን አቋርጦ ለመውጣት በመገደዱም ቀደም ሲል ያላሰበበትን ውሣኔ መወሰኑንና መናገሩንም አመልክቷል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG