በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፄ ኃይለ ሥላሴ የልጅ ልጆች ህገ-መንግስታዊ ዘውድ እንዲቋቋም እያቀነቀኑ ነው


አጼ ኃይለ ሥላሴ መስከረም 2 ቀን 1967 ከስልጣን እስከተወገዱበት ጊዜ ድረስ ኢትዮጵያን ከሃምሣ ዓመታት በላይ ያስተዳደሩ ንጉሥ ነበሩ። የዘውዳዊ አስተዳደሩን የተካው ወታደራዊ አስተዳደር የቀድሞውን የፊውዳል ስርአት ቅሪቶች በሙሉ ከፖለቲካው ዓለም ካስወጣ በኋላ፤ አንዳንዶቹን ሲገድል፣ ሌሎቹን ደግሞ ለእስር፣ ለእንግልትና ለስደት ዳርጓል።

ያኔ ከተሰደዱት መካከል የንጉሣዊው ቤተሰብ አባላት የሆኑት የአጼ ኃይለ ስላሴ የልጅ ልጆች አሉበት። አብዛኞቹ ህጻናት ነበሩ ያኔ ካገር ኮብልለው ሲወጡ። ዛሬ ከሦስት አሥርት ዓመታት በላይ አልፏል፤ የልጅ ልጆቹ አባቶች ሆነዋል፣ አባቶቻቸውና እናቶቻቸው በህይወት የሌሉም አሉ።

በዚህ በዋሽንግተን ዲሲ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያዊያኑ ማህበረሰብ የንጉሱ118ኛ የልደት በአል ባለፈው ዕሁድ ታስቦ ውሏል። ሙሉ ዝግጅቱን ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG