በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀደማዊ ኃይለሥላሴ መታሰቢያ ሃውልትና ታሪካዊ ፋይዳው


የቀደማዊ ኃይለሥላሴ መታሰቢያ ሃውልት
የቀደማዊ ኃይለሥላሴ መታሰቢያ ሃውልት

"የዛሬ ሰባት ዓመት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሃውልት ላይ ጥያቄ መነሳቱ ራሱ ሌሎችን ሳይሆን ቢኖሩ ኖሮ ኩዋሜ ንኩርማን ነበር የሚያስገርመው። ምክኒያቱም እነ ክውዋሜ ንኩርማ ወደ አፍሪቃ አንድነት፣ ወደ አፍሪቃ ነጻነት መጣን የሚሉት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ አረዓያነት ነው።" ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ አንጋፋ የታሪክ መምሕር።

የቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ለአፍሪካ አንድነት ምሥረታና ለአሕጉሪቱ ነጻነት ላበረከቱት አስተዋፅዖ ከአፍሪቃ ሕብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የመታሠቢያ ሃውልት ይቆምላቸው ዘንድ በተደረሰው ውሳኔ መሠረት በቅርቡ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አሕመድና ሌሎች የአህጉሪቱ መሪዎች እንዲሁም የቤተሰባቸው አባላት በተገኙበት ተመርቋል።

ከዓመታት በፊት ለሌላው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት መሥራች ለጋናው የቀድሞ ፕሬዝዳንት ክዋሜ ንኩርማ የመታሰቢያ ሃውልት ሲሰራ ለኢትዮጵያው ንጉሠ ነገሥትም በተመሳሳይ የመታሰቢያ ሃውልት ያለመሠራቱ በጊዜው በእጅጉ ማወዛገቡ አይዘነጋም።

“ለመሆኑ የመታሠቢያ ሃውልቱ መቆም ምን ዓይነት ተጨባጭ ታሪካዊ ፋይዳ ይኖረው ይሆን? አንድምታውስ ምንድነው?” የሚሉትንና ሌሎች መሠረታዊ ጥያቄዎች ከአንድ የታሪክ አዋቂና ለሃውልቱ መቆም አሥፈላጊነት ሲሟገቱ ከነበሩ ወገኖች አንዱን ጋብዘን አወያይተናል።

ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ ለበርካታ ዓመታት በዩናይትድ ስቴትሱ የክሪስቶፈር ኒውፖርት ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምሕር ናቸው። በኩዋሜ ንኩርማና በአፍሪቃዊነት ፍልስፍና ላይ ያተኮረውን ጨምሮ በርካታ የታሪክ ጥናት ጽሁፎችን ጽፈዋል።

ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ
ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ

ነብያት አክሊሉ በዩናይትድ ስቴትስ ተወልዶ ያደገ ወጣት ነው። “ከሁለቱ ዋነኞቹ የአፍሪቃ አንድነት መሥራቾች ቀዳሚ ኃይለሥላሴ ተለይተው የመታሰቢያ ሃውልት ሳይቆምላቸው መቅረቱ ታሪካዊ ሥህተት ነው” በሚል ለዓመታት ከተሟገቱ ወገኖች አንዱ ነው።

አቶ ነብያት አክሊሉ
አቶ ነብያት አክሊሉ

የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።

የቀደማዊ ኃይለሥላሴ መታሰቢያ ሃውልትና ታሪካዊ ፋይዳው
please wait

No media source currently available

0:00 0:20:16 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG