በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ምሥራቅ አራሽ-አርብቶ አደሮችና የሰሞኑ ሰማይ


ሃገያ በመጠኑ እየጣለ ነው፡፡ ተስፋው ያለው ግን የገና ዝናብ ላይ ነው፡፡

በአፍሪካ ቀንዱ የበረታ ድርቅ ከተጠቁት የኢትዮጵያ አካባቢዎች አንዱ የሆነው የቦረና ዞን ከአደጋው የማገገም አጋጣሚ የሚያገኘው ከአምስትና ከስድስት ወራት በኋላ በሚጠበቀው የገና ዝናብ መሆኑን በአካባቢው የሚንቀሣቀስ አንድ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አስታወቀ፡፡

"የራስን ዕድል በራስ ከመወሰን" ፖለቲካዊ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተወክለው አዲስ አበባ የሚገኙ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች ደግሞ በድርቁ ምክንያት በርካታ ከብቶች መሞታቸውን፤ የነበሩት መጠነኛ እርሻዎችም አለማምረታቸውን ተናግረዋል፡፡

ሁለት የዝናብ ወቅቶች ባሉት አካባቢ ሃገያ ተብሎ የሚጠራው የመስከረምና የጥቅምት ዝናብ በመጠኑ መጀመሩን ከሽማግሎቹ አንዱ አቶ ገርቦሌ ጃተኒ አመልክተው ይሁን እንጂ ዝናቡ እምብዛም አርኪ አለመሆኑን ገልፀዋል፡፡

ባለፈው ክረምት ትልቁ ዝናብ ስላልጣለ ወትሮም ቢሆን ይህንን ያህል ግምት የማይሰጠው የአሁኑ ዝናብ የጠፋውን ሣር ሊያበቅል እንደማይችልና እንግዲህ ካሉበት ሁኔታ እንዲያገግሙ ተስፋቸው ያለው ከአምስትና ከስድስት ወራት በኋላ የሚጠበቀው ትልቁ የገና ዝናብ መሆኑን አቶ ገርቦሌ ጃተኒ አመልክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አግሮ-ፓስቸራሊስት የልማት ማኅበር ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ጉዮም የአቶ ግርቦሌን ሃሣብ አጠናክረዋል፡፡

ለተጨማሪ ዝርዝር የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG