በሐዲያ ዞን ሶሮ ወረዳ ግምብቾ ከተማ፣ ካለፈው የካቲት ወር መጨረሻ ጀምሮ በዘፈቀደ ታስረዋል ያሏቸው 14 ወጣቶች አለመፈታታቸውን ቤተሰቦቻቸው እና ነዎሪዎች ተናገሩ፡፡
ታሳሪዎቹ የዋስትና መብት እንደተከለከሉም አመልክተዋል፡፡
ወጣቶቹን የታሰሩት “በዳንጣ ማኅበረሰብ ልማት ማኅበር ምሥረታ ላይ በመሳተፋቸው ነው፤” ያሉት ቤተሰቦቻቸው፣ የወረዳውን አስተዳደር በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ከሰዋል፡፡
የሶሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ዴቶሬ ደግሞ፣ ወጣቶቹ መታሰራቸውን አምነው፣ እየተፈለጉ ያሉ ተጨማሪ የወንጀል ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን አስታውቀዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም