በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሐዲያ ዞን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወጣቶች ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ በዘፈቀድ እንደታሰሩ፣ ቤተሰቦቻቸው እና ነዋሪዎች ተናገሩ።
የእስራቸው ምክንያት፣ በዞኑ አለ የሚሉት ብልሹ አሠራር እንዲታረም፣ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ በወቅቱ እንዲከፈልና የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች በአግባቡ እንዲቀርብ በመጠየቃቸው ነው፤ ሲሉ አስረድተዋል።
በሌላ በኩል፣ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች፣ በመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ የሰላ ትችት ያቀረቡ ወጣቶች ለእስር እንደተዳረጉ የገለጸው፣ የሐዲያ ሚዲያ ሐውስ ባለቤት እና መሥራች፣ የሚዲያ ቁሳቁሶቹ በዞኑ የጸጥታ ኀይሎች እንደተመዘበረበት አስታውቋል።
የወጣቶችን የዘፈቀድ እስር አስመልክቶ፣ ከዞኑ ባለሥልጣናት ምላሽ እና አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት፣ ስልካቸውን ለማንሣት ፈቃደኛ ባለመኾናቸው አልተሳካም።
ይኹንና፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ የሐዲያን ዞን ጨምሮ በክልሉ የመንግሥት ባለሥልጣናት ሥራቸውን እንዳይሠሩ ያውካሉ፤ ያሏቸው 276 ወጣቶች እንደተለዩና የእስር ርምጃ እንደሚወስድባቸው፣ ሰሞኑን በሆሳዕና ከተማ ከኅብረተሰቡ ተወካዮች ጋራ ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም