በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ሽልማት ሊሰጥ ነው


የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሰው እና የፕሮግራሙ አዘጋጆች በጋራ መግለጫ ሲሰጡ
የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሰው እና የፕሮግራሙ አዘጋጆች በጋራ መግለጫ ሲሰጡ

የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ የሙዚቃ ሽልማት ሰኔ 22/ 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ የሀጫሉ ሁንዴሳ በጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ።

በሽልማት ሥነ ስርዓቱ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎችን በአስር ዘርፍ አወዳድሮ ለመሸለም እቅድ መያዙን የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ እና የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ባለቤት ወይዘሮ ፋንቱ ደምሰው ገለፁ።

ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሆነው በጎ አድራጎት ድርጅቱ በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃ የጀመረውን ሥራ ወደ አፍሪካ ለማሳደግ እቅድ እንዳለው ባለቤቱ ጨምረው ገልፀዋል።

የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን የአርቲስቱን ህልም እውን የማድረግና ስሙን ለማስቀጠል ዓላማ እንዳለውም ወ/ሮ ፋንቱ ተናግረዋል።

የሀጫሉ ሁንዴሳ የሙዚቃ ሽልማት በየዓመቱ አርቲስቱ በተገደለበት ቀን ሰኔ 22/2014 ዓ.ም እንደሚከናወንም ከአዘጋጆቹ ለመረዳት ተችሏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።

የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ሽልማት ሊሰጥ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:42 0:00

XS
SM
MD
LG