በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ለትግራይ ቀውስ የፖለቲካ መፍትኄ እንዲገኝ ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ

ትግራይ ውስጥ ያሉት ሁኔታዎች እጅግ አሳሳቢ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ማምሻውን አስታወቁ።

ሁኔታዎቹ የሚያሳዩት ለቀውሱ ወታደራዊ መፍትኄ ያለመኖሩን እንደሆነ የጠቆሙት ጉቴሬሽ ማምሻውን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር መነጋገራቸውንና የተሳኩ ፀብ የማቆም እርምጃዎች እንደሚወሰዱ ተስፋ እንዳላቸው አመልክተዋል።

ሲቪሎች ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ፣ ሰብዓዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው እንዲደርስና የፖለቲካ መፍትኄ እንዲገኝም አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ጥሪ አቅርበዋል።

XS
SM
MD
LG