በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጉራጌ ዞኖች በቀጠለ ግጭት ሰዎች እንደሞቱና አላግባብ እንደታሰሩ ጎጎት አስታወቀ


በጉራጌ ዞኖች በቀጠለ ግጭት ሰዎች እንደሞቱና አላግባብ እንደታሰሩ ጎጎት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:15 0:00

በጉራጌ ዞኖች በቀጠለ ግጭት ሰዎች እንደሞቱና አላግባብ እንደታሰሩ ጎጎት አስታወቀ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ እና በምሥራቅ ጉራጌ ዞኖች በቀጠለው ጥቃት፣ ሁለት ሰዎች እንደተገደሉና ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ 70 ሰዎች ከሕግ አግባብ ውጭ እንደታሰሩ፣ ጎጎት ፍትሕ እና አንድነት ፓርቲ፣ ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ መሐመድ አብራር፣ በጉራጌ ዞን እየተፈጸመ ነው ያሉት የመብቶች ጥሰት፣ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ተናግረዋል፡፡

ከዞኑ ባለሥልጣናት ምላሽ እና አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት፣ ስልካቸውን ባልማንሳታቸው ሐሳባቸው አልተካተተም።

ይኹንና፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ እንዳሻው ጣሰው፣ 276 ሰዎች በሕግ ቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ ያስታወቁትንና ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንደታሰሩ የተናገሩትን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG