በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ ታጣቂዎች 40 ሰዎች ገደሉ


ፕላቱ ግዛት፣ ናይጄሪያ
ፕላቱ ግዛት፣ ናይጄሪያ

በሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ ሞተር ሳይክል የሚነዱ ታጣቂዎች በአንድ የማዕድን አውጪ ማህበረሰብ ላይ ተኩስ በመክፈት እና ቤቶችን በማቃጠል ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 40 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው መንግስት አስታወቀ።

ተራራማ አካባቢ በሆነው ፕላቱ ግዛት፣ ዋሴ ወረዳ። ሰኞ ማለዳ በተፈፀመው ጥቃት ታጣዊቆቹ ዙራክ የተሰኘ፣ በማዕድን በማውጣት የሚተዳደር ማህበረሰብ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን የፕላቶ ግዛት ኮሚሽነር ሙሳ ኢብራሂም አሾምስ ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በስልክ አመልክተዋል።

ዋሴ የተሰኘው አካባቢ ዚንክ እና ሊድ የተሰኙ ማዕድኖች በብዛት የሚገኙበት ሲሆን ፕላቱ ደግሞ በቆርቆሮ ማዕድን በስፋት ይታወቃል።

በብዛት ሙስሊሞች የሚኖሩበት ሰሜናዊው የናይጄሪያ ክፍል እና በብዛት ክርስቲያኖች የሚገኙበት ደቡባዊው የናይጄሪያ ክፍል መለያያ መስመር ላይ የምትገኘው ፕላቱ ግዛት፣ በእረኞች እና በአርብቶ አደር ገበሬዎች መካከል በሚፈጠር አለመግባባት ትታወቃለች።

በአየር ንብረት ለውጥ ከግጦሽ መሬት፣ ከውሃ አቅርቦት እና እንደ ብረት ማዕድን ከመሳሰሉ ሌሎች ሀብቶች ጋር በተያያዘ የሚፈጠረውን ውጥረት አባብሶታል።

አንዳንድ የሰሜን ምዕራብ እና የሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያ አካባቢዎችም በከፍተኛ ሁኔታ በታጠቁ ወንጀለኛ ቡድኖች ገንዘብ ለማግኘት በሚፈጽሟቸው ወረራ እና የጅምላ አፈና ሽብር ውስጥ ወድቀዋል።

በጥር ወር በፕላቱ በሚገኝ ማንጉ ከተማ ውስጥ በተፈፀመ የእርስ በእርስ ግጭት ቤተክርስቲያናት እና መስጊዶች የተቃጠሉ ሲሆን፣ ከ50 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ለስደት ተዳርገዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG