በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ ታጣቂዎች ከ50 ሰዎች በላይ ገደሉ


በናይጄሪያ ማዕከላዊ ሰሜን ግዛት፣ የታጠቁ ሰዎች ትላንት በከፈቷቸው ኹለት ጥቃቶች፣ ቢያንስ 50 ሰዎችን መግደላቸውን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ባለፈው ረቡዕ፣ ቤኑ በሚባለው ግዛት ታጣቂዎች 47 ሰዎችን ሲገድሉ፣ በቀደመው ቀን ደግሞ ሦስት ሰዎችን ገድለዋል፤ ሲሉ፣ የአካባቢው አንድ ባለሥልጣን አስታውቀዋል።

የግዛቲቱ ፖሊስ ተወካይ፣ ጥቃት መፈጸሙን አረጋግጠው፣ ታጣቂዎቹ አንድ የገበያ ሥፍራን ዒላማ እንዳደረጉ ገልጸዋል። የሟቾቹ ቁጥር ግን ስምንት ብቻ መኾኑን ተናግረዋል።

የጥቃቱ መነሾ ወዲያውኑ ግልጽ ባይኾንም፣ ባለሥልጣናት ግን፣ በአርብቶ አደሮች እና በአርሶ አደሮች መሀከል፣ በግጦሽ መሬት ይገባኛል ጥያቄ ሳቢያ የተፈጠረ ሊኾን እንደሚችል ይጠረጥራሉ። አርብቶ አደሮቹ እንስሶቻቸውን በማሠማራት ግጦሻቸውንና ሰብላቸውን እንዳወደሙባቸው አርሶ አደሮቹ ይናገራሉ።

ለምለም እና የዳቦ ቅርጫት እንደኾነ የሚነገርለት የናይጄሪያ ሰሜናዊ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ክፍል፣ በአርብቶ አደሮች እና በአርሶ አደሮች መሀከል ለረጅም ጊዜ ግጭት ሲካሔድበት ቆይቷል። በግጭቱ ምክንያት፣ ምርት በየጊዜው እያሽቆለቆለ መኾኑን አሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ ጠቁሟል።

XS
SM
MD
LG