በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ሁኔታ


በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ድባጢ ወረዳ፣ ትናንት የታጠቁ ሃይሎች ንፁሃን ዜጎችን መግደላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።

የክልሉ መንግሥት ኮሙኒኬሽንስ ጉዳዮች ሃላፊ አቶ መለሰ በየነ "ንፁሃን ዜጎች ላይ ዘግናኝ ጥቃት ተፈፅሟል። ጥቃት ፈፃሚዎቹ ከህወሓት የጥፋት ተልእኮ የተሰጣቸው ናቸው" ብለዋል።

ሃላፊው ጥቃቱን የፈፀሙት የቤኒሻንጉል ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ አባላት ናቸው ቢሉም ከድርጅቱ ለማረጋገጥ አልተቻለም።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፀጥታና ደኅንነትን ለማጠናከር ፈጣንና የተቀናጀ እርምጃ አስፈላጊ ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፀጥታ ሁኔታ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00


XS
SM
MD
LG