በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይጄሪያ ታጣቂዎች 32 ሰዎችን ጠለፉ


ፎቶ ፋይል፦ አቡጃ- ካዱና ባቡር ጣቢያ አቡጃ፣ ናይጄሪያ እአአ 12/2022
ፎቶ ፋይል፦ አቡጃ- ካዱና ባቡር ጣቢያ አቡጃ፣ ናይጄሪያ እአአ 12/2022

በደቡብ ናይጄሪያ ታጣቂዎች በአንድ የባቡር ጣቢያ ላይ ጥቃት ከፍተው 32 ስዎችን አፍነው ሲወስዱ ሌሎች በርካቶችን ማቁሰላቸውን ፖሊስና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በናይጄሪያ ሰዎችን አግቶ ቤዛ መጠየቅ ትልቅ ችግር እየሆነ መምጣቱን የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

ከሌጎስ 360 ኪ.ሜ ላይ በሚገኘው ኤዶ ግዛት ውስጥ ባለ የባቡር ጣቢያ ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከከፈቱ በኋላ ባቡር ጥበቃ ላይ የነበሩ 32 ችሰዎችን አፍነው ወስደዋል ሲል ፖሊስ አስታውቋል። አንድ ሰው ግን ማምለጥ መቻሉን ፖሊስ ጠቁሟል።

ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ታጣቂዎች በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ሃዲዱን በቦምብ አፍርሰው በባቡሩ ላይ ጥቃት ሲከፍቱ 8 ሰዎች ሞተዋል። በደርዘን የሚቆጠሩ ተሳፋሪዎችንም አግተዋል።

ከስምንት ወርና የመጨረሻዎቹ ታጋቾች ከተለቀቁ በኋላ የባቡር መሥመሩ እንደገና ተከፍቷል።

XS
SM
MD
LG