በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ናይጄሪያ ውስጥ ተማሪዎች በታጣቂዎች ተጠለፉ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ሰሜን ማዕከላዊ ናይጄሪያዋ ናይጀር ክፍለ ሃገር ከሚገኝ የእስልምና ትምህርት ቤት ውስጥ ታጣቂዎች ተማሪዎችን መጥለፋቸውን ፖሊሶች እና የክፍለ ሃገሩ ባለሥልጣናት አስታወቁ።

ባለፉት ቅርብ ወራት ታጣቂ ቡድኖች ሰሜን ናይጄሪያ ውስጥ ከየትምህርት ቤቱ እና ከየዩኒቨርስቲው ማስለቀቂያ ገንዘብ ለመቀበል ተማሪዎችን በተደጋጋሚ እየጠለፉ እንደሆን እና ካለፈው ታህሳስ ወዲህ ቁጥራቸው ከሰባት መቶ በላይ ተማሪዎች እንደተጠለፉ ተገልጿል።

አጥቂዎቹ ትምህርት ቤቱን ወርረው ባገኙት ላይ እየተኮሱ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተመሪዎችን ይዘው ሄደዋል ሲሉ የአካባቢው አስተዳደር ቃል አቀባይ ገልጸዋል፥ በቅርብ ወራት አብዛኞቹ ተማሪዎች የተጠለፉት ከአዳሪ ትምህርት ቤቶች እንደነበር ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG