በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

75ኛው የጉጂ ገዳ ኦሮሞ አስተዳደር የርክክብ ሥነ ሥርዓት ተጠናቀቀ


አዲስ ሥልጣን የተረከቡት አባ ገዳ ጃርሶ ዱጎ።
አዲስ ሥልጣን የተረከቡት አባ ገዳ ጃርሶ ዱጎ።

በመዔ ቦኮ ሲደረግ የቆየው 75ኛው የጉጂ ገዳ ኦሮሞ አስተዳደር የርክክብ ሥነ ሥርዓት ተጠናቋል።

ካለፈው የካቲት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለስድስት ቀናት የተለያዩ የሥርዓት ማቅናት መርሐ ግብሮች ከተከናወኑ በኋላ፣ ላለፉት ስምንት ዓመታት የጉጂ ገዳ ሥርዓትን ሲመሩ የነበሩት አባ ገዳ ጅሎ መንድኦ ሥልጣናቸውን ለአዲሱ አባ ገዳ ጃርሶ ዱጎ አስተላልፈዋል።

የጉጂ ዞን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ድንቁ፣ በሥልጣን ርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ፣ ኬንያንና ሶማሊላንድን ጨምሮ ከአጎራባች ሀገራት እና ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በሚሊዮኖች ይገመታሉ ያሏቸው እንግዶች እንደታደሙ አስታውቀዋል። ዝግጅቱ ያለምንም የጸጥታ ችግር እንደተፈጸመም አክለው ገልጸዋል።

ሥልጣን የተረከቡት አባ ገዳ ጃርሶ ዱጎ፣ 75ኛው የጉጂ አባ ገዳ ኾነው ለሚቀጥሉት ስምንት ዓመታት የጉጂ ገዳ ኦሮሞ ሥርዓትን ይመራሉ፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG