የኦሮሚያ ክልል ዞኖች እንደ ዐዲስ ከመደራጀታቸው ጋራ ተያይዞ የተፈጠረው ውዝግብ፣ እስከ አሁን እልባት አላገኘም፤ ሲሉ፣ የጉጂ ዞን ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።
በተለይ፣ የጎሮ ዶላ ወረዳ ወደ ምሥራቅ ቦረና መካለሉ፣ የወረዳውን ነዋሪዎች አስቆጥቶ የተቃውሞ ሰልፍ አስወጥቷል፤ ሲሉ፣ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የጎሮ ዶላ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌቱ ጬሉቄ፣ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ ሰሞኑን በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ፥ ንብረት ወድሟል፤ የትራንስፖርት አገልግሎትም ተቋርጧል፤ ሲሉ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሺመልስ አብዲሳ፣ ስለ አደረጃጀት ለውጡ፣ ሰሞኑን በጨፌ ኦሮሚያ አባላት ተጠይቀው፣ ወደ ኋላ የሚመለስ መዋቅር የለም፤ ሲሉ አብራርተዋል።
ሙሉ ዘገባን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም