በጊኒ ኮናክሪ በእግር ኳስ ጨዋታ መካከል በተነሳ ግጭት 56 ሰዎች በመረጋገጥ ሕይወታቸው ሲያልፍ ከ10 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መጎዳታቸውን ባለሥልጣናት ተናገሩ፡፡
የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኦውሪ ባህ ትላንት ማምሻውን በኤክስ ማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ላይ ባወጡት ጽሁፍ በንዝሮኮሬ ከተማ በላቤ እና ንዝኮሬ ቡድኖች መካከል ትላንት እሁድ ከሰዓት በኋላ በተካሄደው የሀገር ውስጥ የኳስ ጨዋታ ላይ በተከሰተው ግጭት ሰዎች ተረጋግጠው መሞታቸውን እና መጎዳታቸውን አመልክተዋል፡፡
የሀገር ውስጥ መገናና ብዙሃን ረብሻው የተጀመረው የፍጹም ቅጣት ምት በመሰጠቱ የተበሳጩ ደጋፊዎች ወደ ሜዳ ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ መሆኑን ዘግበዋል፡፡
የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ፋና ሱማህ በሰጡት መግለጫ ለአደጋው ተጠያቂ የሆኑትን ለማጣራት ባለስልጣናት ምርመራ እያደረጉ ነው ብለዋል።
ከተጎጂዎች መካከል በርካታ ህጻናት እንደሚገኙ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት አስታውቀዋል፡፡
የጊኒው ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኦሪ ባህ በኤክስ መድረክ ላይ እንደተናገሩት ውድድሩ የተካሄደው ለሀገሪቱ ወታደራዊ መሪ ማማዱ ዱምቦያ ክብር ለመግለጽ ነበር፡፡
መድረክ / ፎረም