በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጊኒው ጁንታ የቀድሞው ፕሬዚዳንት “ከአገር አይወጡም” አለ


በመፈንቅለ መንግስት የተወገዱት የቀድሞ ጊኒ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ
በመፈንቅለ መንግስት የተወገዱት የቀድሞ ጊኒ ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ

በቅርቡ በጊኒ መንፈንቅለ መንግስት ያካሄደው ወታደራዊ ጁንታ፣ ከምዕራብ አፍሪካ መሪዎች የተጣለበት ማዕቀብ እንደማያንበረክከው በመግለጽ፣ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ከአገር እንዲወጡ የማይፈቅድ መሆኑን አስታውቋል፡፡

የምዕራብ አፍሪካ አገራት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ህብረት፣ በጊኒ ወታደራዊ መሪዎችና ንብረቶቻቸው ላይ ባለፈው ሀሙስ ማዕቀብ ጥሏል፡፡

በማግስቱም የአይቮሪ ኮስትና የጋና መሪዎችም፣ በመፈንቅለ መንግሥቱ የተወገዱት ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ ከአገር እንዲወጡ እንዲፈቅድላቸው ለማግባባት ጊኒ ገብተው እንደነበር ተዘግቧል፡፡

የጁንታው መሪዎች ግን፣ በአገሪቱ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ፣ አልፋ ኮንዴ ከአገር እንደማይወጡ ጠቅሰው፣ “ጊኒ ለማንም የውጭ ኃይል አትንበረክክም” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG